🗳️ 🇪🇹 ለሀገር እና ለሕዝብ ይጠቅማል ያሉትን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የአምበር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

20

 

ደብረ ማርቆስ፡ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት ዝግጁ መኾናቸውን በምሥራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ የአምበር ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መብታቸውን ተጠቅመው ይበጀናል ለሚሉት ድምፃቸውን ለመስጠት ዕለቱን እየተጠባበቁ መኾኑን ነው የተናገሩት፡፡

በምርጫ ካርዳቸው ለሀገር እና ለሕዝብ ይበጃል ለሚሉት ድምጻቸውን በመስጠት ጠንካራ እና ቅቡልነት ያለው መንግሥት እንዲረጋገጥ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹት ነዋሪዎቹ በዚህም ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን እየተጠባበቁ መኾናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ምርጫ ዜጎች የሀገራቸውን መንግሥት በራሳቸው ድምጽ የሚመርጡበት እና በዜጎች ፍላጎት ላይ መሠረት ያደረገ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የሚያስችል መኾኑንም አስረድተዋል፡፡

ነዋሪዎቹ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #ምሥራቅ_ጎጃም_አምበር_ከተማ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ግብረወርቅ ጌታቸው

የአሚኮ ዲጅታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየፍኖተ ሰላም ከተማ የምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭቱን አጠናቅቋል።
Next articleበሰሜን ሸዋ ዞን ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲከናወን ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቅቋል።