🗳️ 🇪🇹 ለሀገር እና ለአካባቢያቸው ይጠቅማል ያሉትን በካርዳቸው ለመወሰን መዘጋጀታቸውን የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

9

 

ሰቆጣ፡ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ይጠቅማል ያሉትን በካርዳቸው ለመወሰን ቀኑን እየጠበቁ እንደሚገኙ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎቹ ዲያቆን እንዳለው ታከለ እና አቶ ታረቀኝ ተስፋዬ ከዚህ በፊት ሦሥት ጊዜ ምርጫ ላይ መሳተፋቸውን ገልጸዋል።

ለአራተኛ ጊዜ የሚሳተፉበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተለየ ድባብ ያለው በመኾኑ ምርጫው ኢትዮጵያ ካሳለፈቻቸው ምርጫዎች የተሻለ ምርጫ የምታካሄድበት ሊኾን እንደሚችል ያላቸውን ዕምነት አንስተዋል።

የሀገርን ልማት የሚያፋጥን እና አንድነትን የሚያጸና ፓርቲን ለመምረጥ እና በካርዳቸው ለመወሰን መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት።

ሌላኛዋ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ ወይዘሪት አድና ጥጋቡ ከአሁን በፊት በዕድሜ አለመድረስ ምክንያት መርጣ እንደማታውቅ ተናግራለች።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግን ለመሳተፍ መዘጋጀቷን ገልጻለች። በዕለቱ በማለዳ ቀድማ ድምጿን እንደምትሰጥም ተናግራለች።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #ዋግኽምራ_ሰቆጣ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰአሚኮ_ዜናብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየምርጫ ጣቢያዎች በጎንደር ከተማ እየተሰናዱ ነው።
Next article“የጸጥታ ኃይሉ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው” እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)