🗳️ 🇪🇹በደብረ ማርቆስ ከተማ የምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ተሠራጭቶ ተጠናቅቋል።

9

 

ደብረማርቆስ፡ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ምርጫ ክልል በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁሶች በአግባቡ መሰራጨታቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አንሙት መንግሥት ተናግረዋል፡፡

በከተማ አሥተዳደሩ በአራቱም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት መከናወኑን ነው የገለጹት፡፡

ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን የሚያስችሉ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መጠናቀቃቸውን የገለጹት አስተባባሪው የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ታዛቢዎች እና ቅሬታ ሰሚዎች በአግባቡ ኀላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውንም አብራርተዋል፡፡

ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ ድምጽ የመስጠት ሂደቱ እንደሚጀመርም ተናግረዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #ደብረ_ማርቆስ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰአሚኮ_ዜናብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“መብታችን ተጠቅመን ለመምረጥ በመዘጋጀታችን ደስተኞች ነን” አካል ጉዳተኞች
Next article🗳️ 🇪🇹 ድምጽን ለሀገር ግንባታ፣ አንደበትን ደግሞ ለሰላም ማስፈኛ መጠቀም ይገባል።