“መብታችን ተጠቅመን ለመምረጥ በመዘጋጀታችን ደስተኞች ነን” አካል ጉዳተኞች

4

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ አሚኮ ያነጋገራቸው አካል ጉዳተኞች ምርጫን ጨምሮ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳታፊ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በተካሄዱ ምርጫዎችም ተሳታፊ እንደነበሩ አስታውሰዋል።

እበዬ ሲሣይ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሦሥተኛ ተከታታይ ጊዜ የሚሳተፉበት መኾናቸውን ተናግረዋል።

ታምራለች እንደሻው ዘንድሮ ለሦሥተኛ ጊዜ በምርጫ እንደሚሳተፉ ገልጸዋል። ምርጫ አንደኛው መብታችን በመኾኑ መሳተፌን አላቆምም ነው ያሉት።

ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄዱ ምርጫዎች እንደተሳተፉ የነገሩን ደግሞ ምትኩ ቢክስ ናቸው። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ የሚሳተፈበት መኾኑን ተናግረዋል።

ባለፉት ምርጫዎች መሳተፍ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተሻለ ትኩረት የተሰጠው፤ መራጮች ስለምርጫ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የተደረገበት እና ይበጃል የሚሉትን በነጻነት የሚመርጡበት ዕድል እንደኾነም አንስተዋል።

“መብታችን ተከብሮ በምርጫ ለመሳተፍ እና የሚበጀንን እንድንመርጥ በመዘጋጀታችን ደስተኞች ነን” ብለዋል።

ከራሳቸው አልፎ በከተማዋ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች በምርጫ ተሳታፊ እንዲኾኑ እና መብታቸውን እንዲጠቀሙ ግንዛቤ ሲፈጥሩ መቆየታቸውንም ተናግረዋል።

#አሚኮ_ዜና #ምርጫ_2018
#ደብረ-ታቦር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰአሚኮ_ዜናብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ ገለልተኛነት እና ግልጽነት የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማዕዘኖች ናቸው።
Next article🗳️ 🇪🇹በደብረ ማርቆስ ከተማ የምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ተሠራጭቶ ተጠናቅቋል።