🗳️ ገለልተኛነት እና ግልጽነት የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማዕዘኖች ናቸው።

6

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና ስኬታማ ኾኖ ይጠናቀቅ ዘንድ በድምፅ መስጫ ቀን በምርጫ ጣቢያ አካባቢ የሚገኙ አካላት ጉልህ ሚና አላቸው።

ለመኾኑ በድምፅ መስጫ ቀን በምርጫ ጣቢያዎች ከመራጮች ባለፈ እነማን ይገኛሉ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መመሪያ እንደሚደነግገው ከመራጮች ባለፈ በምርጫ ጣቢያዎች አምስት የተለያዩ አካላት መገኘት ይችላሉ ይላል።

ከእነዚህ አካላት ውጭ በምርጫ ጣቢያዎች መገኘት የተከለከለ ስለመኾኑም ያነሳል።

በምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ አካላትም፦ 👇

🗳 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሰማራቸው የምርጫ ጣቢያ አሥፈጻሚዎች፤

🗳 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩ ተወዳዳሪ ወኪሎች፤

🌍 በቦርዱ ፈቃድ የተሰጣቸው የሀገር ውስጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች፤

🎙️በቦርዱ ፈቃድ የተሰጣቸው የመገናኛ ብዙኀን አካላት እና

👮‍♂️ አስፈላጊ በኾነ ጊዜ በምርጫ ጣቢያ አሥፈጻሚዎች ጥሪ የሚቀርብላቸው የጸጥታ አካላት እንደሚገኙ ይጠቅሳል።

#አሚኮ_ዜና #ምርጫ_2018 #አማራ #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleሕዝብ እና ሀገርን የሚጠቅመውን ፓርቲ መዝነው ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የጃዊ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።