
እንጅባራ፡ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጃዊ ወረዳ እና የፈንድቃ ከተማ አርሶ አደሮች ለአርሶ አደሩ እና ለሀገር በቀጣይነት ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
አርሶ አደር በለጠ ኃይሉ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የምርጫ ቀንን እየተጠባበቁ መኾናቸውን ጠቁመዋል። ባወጡት ካርድ በቀጣይ ሕዝብን እና ሀገርን የሚጠቅም፣ ለግብርናም ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ፓርቲ መዝነው ለመምረጥም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
የጃዊ ወረዳ ወርቅሀገር ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር ክንዴ ተገኘ እና የዴቅ ዘረ ገነት ቀበሌ ነዋሪው አርሶአደር አሳዬ ንጋቱ እንዳሉት የገጠሩ ማኅበረሰብ የፓርቲዎችን የቅስቀሳ ሂደት በአግባቡ ሲከታተል በመቆየቱ የሚመርጠውን ፓርቲ ለመለየት በቂ ግንዛቤ አግኝቷል።
ግንቦት 24 አርሶ አደሮች ለራሳቸው የሚበጀውን የሚመርጡበት ታሪካዊ ቀን መኾኑንም ጠቁመዋል። በወሰዱት ካርድ በዕለቱ ወጥተው ለሚበጃቸው ድምጽ እንደሚሰጡም ነው የተናገሩት።
ምርጫው በሰላም እንዳይካሄድ የሚፈልጉ አካላት የሚነዙትን ወሬ እንደማይሰሙ እና በምርጫው ዕለት ሂደቱ ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ከጸጥታ አካላት ጋር ያላቸውን ቅንጅታዊ አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አርሶ አደሮቹ በቁርጠኝነት ተናግረዋል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #አርሶ_አደሮች #አዊ_አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ፦ ሰለሞን ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰአሚኮ_ዜናብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
