
ወልድያ፡ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምርጫው ስኬታማ ኾኖ ይጠናቀቅ ዘንድ በቅንጅት እየተሠራ መኾኑን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ አስታውቋል።
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማነት በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የተናገሩት የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ደርበው አዳነ ናቸው።
ባለ ድርሻ አካላትን ያካተተ ግብረ ኃይል ተደራጅቶ ከመራጮች ምዝገባ ጀምሮ ምርጫው ስኬታማ እንዲኾን በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነውም ብለዋል።
የከተማዋን ነዋሪዎች እና “የመራጮችን ሰላም ለማረጋገጥ በልዩ ጥንቃቄ እና በቅንጅት እየሠራን እንገኛለን” ብለዋል መምሪያ ኀላፊው።
የጸጥታ ኃይሎች የሚያደርጉት ጥረት እንዲሳካ ኅብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ተባባሪ እንዲኾንም ጥሪ አቅርበዋል።
#አሚኮ_ዜና #ምርጫ_2018
#ወልድያ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
