
ደሴ: ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
በዚህ የምርጫ ዕለት በወሰዱት ካርድ ይወክለናል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
“በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫን እንደሚያካሂዱም” ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በዚህም በጠቅላላ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት።
ሀገር የምትገነባው እኛ በሰጠነው ድምጽ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ የተሰጠንን ዕድል በአግባቡ መጠቀም አለብን ብለዋል።
#አሚኮ_ዜና #ምርጫ_2018
#ደሴ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
