ምርጫ ዜጎች ለሚወዷት ሀገር ሲሉ የሚተገብሩት ነው።

9

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚደረጉ ዝግጅቶች በየአካባቢው ተጠናክረው ቀጥለዋል።

የሰሜን ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያም ምርጫው ስኬታማ ኾኖ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

የመምሪያው ኀላፊ ገብረ ሥላሴ ታዘብ የምርጫው ሂደት ደኅንነቱ የተጠበቀ እንዲኾን የዞኑ የጸጥታ ኃይል ከክልሉ እና ከፌዴራል የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በቅንጅት እየሠራ ነው ብለዋል።

በዞኑ በሚገኙ የምርጫ ክልሎች እና የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ያለምን የጸጥታ ችግር ወደሚፈለገው የማድረስ ሥራ ሥለመከናወኑም አንስተዋል።

የምርጫ ቦርድ ሕግን በጠበቀ መንገድ በምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ ኃይሉ ስምሪት ተሰጥቶት እየተሠራ እንደኾነ ነው የገለጹት።

ዘጋቢ:- ዘመኑ ይርጋ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰአሚኮ_ዜናብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleበሰሜን ወሎ ዞን አንጎት ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።
Next article“በዕውቀት ላይ ተመሥርተን እንመርጣለን” የደሴ ከተማ ነዋሪዎች