ለስኬታማ የምርጫ ሂደት የማኅበረሰቡ ሚና ጉልህ ነው።

6

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲኾን በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ተሾመ ብዙ በምርጫ ወቅት የፖሊስ ሚናን እና የምርጫ ሕግጋትን የተመለከተ ሥልጠና ለፖሊስ መሪዎች እና አባላት መሰጠቱን ገልጸዋል።

የምርጫ ቁሳቁስን እና የጣቢያዎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኀላፊነትን በብቃት ለመወጣት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በገለልተኝነት ለሁሉም ወገኖች ዕኩል አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ ነው ብለዋል።

ለሰላም መስፈን የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመኾኑ በርካታ የሕዝብ መድረኮች መፈጠራቸውንም ተናግረዋል።

ኅብረተሰቡ በሰላም አደረጃጀት በመሳተፍ እና መረጃ በመስጠት ከፖሊስ ጎን እንዲቆምም ጠይቀዋል።

ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየባሕል ፍርድ ቤቶች ግጭትን በዕርቅ የሚያጸኑ፣ ቁርሾ እና ቂምን የሚሽሩ ናቸው” አቶ ዓለምአንተ አግደው
Next article” ‘መንገድ ተዘግቷል’ በሚል የሚራገበው ፕሮፖጋንዳ የጽንፈኛ ኃይሉ የተለመደ የሐሰት ወሬ ነው” እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)