“መብታችን ተጠቅመን ድምጻችን ለመስጠት ተዘጋጅተናል” የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች

7

 

ጎንደር: ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምርጫ ካርዳቸውን ተጠቅመው ድምጽ ለመስጠት ዕለተ ሰኞን እየጠበቁ መኾኑን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

በጎንደር ከተማ ነዋሪነታቸውን ካደረጉ አስተያየት ሰጭዎች መካከል 10 አለቃ ጌጡ ይስማው የምርጫ ካርዳቸውን አስቀድመው ማውጣታቸውን ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

‎ለሀገር እድገት ይጠቀማል የሚሉትን ፓርቲ በመምረጥ መብታቸውን ለመጠቀም የምርጫውን ቀን በመጠባበቅ ላይ መኾናቸውንም አንስተዋል።

‎ዜጎች የምርጫ ካርዳቸውን መጠቀም አለባቸው ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ የሽመቤት ጸጋው ናቸው።

‎ከዚህ በፊት የመምረጥ ልምድ እንደነበራቸው ያጫወቱን ነዋሪዋ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።

ምርጫው ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ በኾነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።

#አሚኮ-ዜና #ጎንደር #ምርጫ-2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ አዲስ አለማየሁ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ 🇪🇹 በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው።
Next articleየባሕል ፍርድ ቤቶች ግጭትን በዕርቅ የሚያጸኑ፣ ቁርሾ እና ቂምን የሚሽሩ ናቸው” አቶ ዓለምአንተ አግደው