🗳️ 🇪🇹 በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው።

7

 

ሰቆጣ፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለምርጫው ቁሳቁስ እየተሰራጨ መኾኑን የምርጫ ክልሉ ገልጿል።

የሚሰራጩት የምርጫ ቁሳቁስም የድምጽ መስጫ ሳጥኖች፣ ልዩ ልዩ የምርጫ ወረቀቶች፣ መራጮች በምስጢር የሚመርጡባቸው መከለያዎች እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች ናቸው።

የምርጫ ቁሳቁሱን ያለምንም ችግር ወደ ምርጫ ጣብያዎች በመጓጓዝ እና ለመራጮች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የጸጥታ መዋቅሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራውን አጠናክሮ መቀጠሉንም የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አምበሉ ጥላሁን ጠቅሰዋል።

ዘጋቢ፦ደጀን ታምሩ

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ሞርጫ_2018 #ዋግኸምራ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🗳️ 🇪🇹በእንጅባራ የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት ሥራ እየተከናወነ ነው።
Next article“መብታችን ተጠቅመን ድምጻችን ለመስጠት ተዘጋጅተናል” የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች