🗳️ 🇪🇹በእንጅባራ የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት ሥራ እየተከናወነ ነው።

6

 

እንጅባራ፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በ “ኮሶበር” የምርጫ ክልል ለምርጫው የሚውሉ ቁሳቁሶችን ወደየምርጫ ጣቢያዎች የማሠራጨት ሼል እየተከናወነ ይገኛል።

የኮሶበር የምርጫ ክልል ኀላፊ አንሙት እምቢአለ ምርጫውን በስኬት ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የምርጫ አሥፈፃሚዎች አስፈላጊው ሥልጠና ተሰጥቷቸው በየምርጫ ጣቢያው መግባታቸውን እና ሥራ መጀመራቸውን አብራርተዋል።

የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እና አስተማማኝ እንዲኾን የጸጥታ ኀይሎች በየምርጫ ጣቢያው የተመደቡ ሲኾን፣ ለምርጫው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችም ወደየጣቢያዎቹ በወቅቱ እየተሰራጩ ይገኛሉ።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ሞርጫ_2018 #አዊ_ኮሶበር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ :- በቃሉ ፈረደ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የፓን አፍሪካ ኤችአይቪ ክሊኒሻኖች ማኅበር መመስረት አህጉራዊ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል ይሰጣል” ዶክተር መቅደስ ዳባ
Next article🗳️ 🇪🇹 በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው።