“የፓን አፍሪካ ኤችአይቪ ክሊኒሻኖች ማኅበር መመስረት አህጉራዊ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል ይሰጣል” ዶክተር መቅደስ ዳባ

7

 

አዲስ አበባ፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፓን አፍሪካ ኤች አይ ቪ ክሊኒሻኖች ማኅበር የመጀመሪያው ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ​ የፓን አፍሪካ ኤች አይ ቪ ክሊኒሻኖች ማኅበር መቋቋም አፍሪካ በኤች አይ ቪ እና በተያያዙ የሕዝብ ጤና ተግዳሮቶች ላይ በሚደረገው ትግል ሳይንሳዊ አመራሯን፣ ክሊኒካዊ ብቃቷን፣ የዕውቀት ልውውጧን እና ቀጣናዊ ትብብሯን ለማጠናከር ለምታደርገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መኾኑንም አንስተዋል።

የማኅበሩ መመሥረት በክሊኒካዊ ልህቀት አህጉራዊ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል ይሰጣልም ብለዋል።

​የኢትዮጵያ መንግሥት በዘርፉ ፈጠራን ለማስፋት፣ የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር እና ኤች አይ ቪ ኤድስን እንዲሁም ተያያዥ የሕዝብ ጤና ስጋቶችን ለማስቆም የሚደረገውን ጉዞ ለማፋጠን ከማኅበሩ እና ከሚመለከታቸው ጋር በቅንጅት ለመሥራት የፓለቲካዊ ቁርጠኝነት እንዳለው ተናግረዋል።

የማኅበሩ ሊቀመንበር ዶክተር ሙሀንግዊ ሙላኡድዚ የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመቆጣጠር እና አስፈላጊውን ሕክምና ተደራሽ ለማድረግ በአፍሪካውያን ለአፍሪካውያን የተዘጋጀ የጤና ሥርዓትን እና መፍትሄን መተግበር ወሳኝ ነው ብለዋል።

ማኅበሩ አፍሪካውያን ቴክኒሻኖች ድምፃቸውን በጋራ የሚያሰሙበት፤ ለሚመጣው ትውልድ አህጉራዊ ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ አፍሪካን ለማውረስ የፓን አፍሪካ ኤች አይ ቪ ክሊኒሻኖች ማኅበር ተስፋን የሚሰጥ ነውም ብለዋል።

በጉባኤው የተለያዩ ጥናታዊ ጹሑፎችም ቀርበዋል።

#አሚኮ_ዜና #የፓን_አፍሪካ_ኤችአይቪ_ክሊኒሻኖች_ማኅበር #አዲስ_አበባ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🗳️ 🇪🇹 በምዕራብ ጎንደር ዞን የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው።
Next article🗳️ 🇪🇹በእንጅባራ የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት ሥራ እየተከናወነ ነው።