
እንጅባራ፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ ኾኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር አስራት ምትኩ ለምርጫው ስኬታማነት የጸጥታ ሥራው በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫው ዕለት እና ከምርጫ በኋላ የሚከናወኑ ተግባራት ተለይተው አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።
ምርጫው ስኬታማ ይኾን ዘንድ የጸጥታ ኃይሎች በየአካባቢያቸው ስምሪት መውሰዳቸውንም ገልጸዋል።
ማኅበረሰቡም ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን በመሰለፍ እና የቀደመ የአብሮነት እና የመተባበር እሴቱን የበለጠ በማጠናከር ለምርጫው ስኬታማነት እያገዘ ነው ብለዋል።
በቀጣይም ለጸጥታ መዋቅሩ መረጃ የመስጠት እና የመተባበር ልምዱን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
#አሚኮ-ዜና #አዊ #ምርጫ2018 #አማራ #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ፦ በቃሉ ፈረደ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
