🗳️ 🇪🇹 ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ የሰሜን ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ዝግጁ ነው።

18

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ​የግንቦት 24/2018 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ በኾነ መንገድ ለማጠናቀቅ የሚያስችል ቅድመ-ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ተግባር መገባቱን የሰሜን ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የሰሜን ጎጃም ዞን ፖሊስ መምርያ አዛዥ ኮማንደር በሪሁን አየነው የምርጫውን ሂደት ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ከፌዴራል የጸጥታ ኀይል ጋር በቅንጅት የሚሠራ የምርጫ ግብረ-ኀይል በዞን እና በወረዳ ደረጃ ተቋቁሞ ወደ ስምሪት ተገብቷል ብለዋል።

​በዞኑ ስር በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች እና ሦሥት የከተማ አሥተዳደሮች ውስጥ ባሉ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ለጸጥታ አባላት ተልዕኮ ተሠጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ሕዝቡ በሰላም ድምጹን መስጠት እንዲችልም የጸጥታ አካላቱ ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል ነው ያሉት።

ማኅበረሰቡን እና ወጣቶችን ያሳተፉ ሰፊ የቅንጅት ሥራዎች መከናወናቸውንም ኮማንደር በሪሁን ገልጸዋል።

​”የጸጥታ መዋቅሩ ነጻ እና ገለልተኛ በመኾን ሕዝቡ በነጻነት እንዲመርጥ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል” ነው ያሉት።

ሂደቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነው። በቀጣይም ሕዝብን ያሳተፈው የሰላም ማጽናት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ሞርጫ_2018 #ባሕር_ዳር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበስድስቱም ምርጫዎች የተሳትፉት፤ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተዘጋጁት የጎንደር ከተማ ነዋሪ 🗳🇪🇹
Next articleማኅበረሰቡ የመተባበር ባሕሉን በማጠናከር ለምርጫው ስኬታማነት እየሠራ ነው።