
ጎንደር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ወይዘሮ ፀሐይወርቅ አባተ ይባላሉ። በጎንደር ከተማ ነዋሪ ናቸው። 📚 👨🏫 ለ40 ዓመታት በመምህርነት ሙያ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
አሁን ላይ በጡረታ ላይ ይገኛሉ። ልጆቻቸውን አስተምረው እስከ ፕሮፌሰርነት መዓረግ የደረሱ ልጆችም እንዳሏቸው አጫውተውናል።🎓
ባለፉት ጊዜያት በኢትዮጵያ በተካሄዱት በስድስቱም ምርጫዎች ተሳትፏቸው የላቀ እንደነበር ነግረውናል። በስድስቱም ምርጫዎች የሚበጃቸውን በመምረጥ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የራሳቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ወይዘሮ ፀሐይወርቅ እንደገለጹት ለ7ኛ ጊዜ ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫም ካርዳቸውን አውጥተው ለቀጣዩ አምስት ዓመታት የሚበጃቸውን ለመምረጥ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ን በጉጉት እየጠበቁ ነው።
የ64 ዓመት የዕድሜ ባለ ጸጋ የኾኑት እኒሁ እናት በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ዛሬም በአዛውንትነት ዕድሜያቸው ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር በምርጫ ለማሳየት በዝግጅት ላይ መኾናቸውን ነው የተናገሩት።
ምርጫ መምረጥ ማለት መብትን መጠቀም፣ ነጻነትን በመረጡት አካል ማስከበር እና መተዳደር ነው ይላሉ።
ትክክለኛውን የዴሞክራሲ መንገድ ለመከተል ምርጫ ወሳኝ መኾኑንም ከራሳቸው አልፎ ለልጆቻቸው እና በዙሪያቸው ላሉት ሰዎችም እያስተማሩ እንደኾነ ሀሳባቸውን አጋርተውናል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ሞርጫ_2018 #ጎንደር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
