🗳️ በመካነ ሰላም ከተማ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ለማጠናቀቅ የጸጥታ ኃይሉ ዝግጁ ነው።

13

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የጸጥታ ኃይሉ በቅንጅት እየሠራ መኾኑን የመካነ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

የጽሕፈት ቤት ኀላፊው 10 አለቃ ደርቤ ገበየሁ በከተማዋ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን በመጠበቅ እና የከተማዋን ሰላም በማጽናት ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የጸጥታ ኀይሉ ዝግጁ መኾኑን ተናግረዋል።

የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭቱን ጤናማ በማድረግ እና የምርጫ ሂደቱን ሰላማዊ በማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንደኾነ ነው የገለጹት።

ማኅበረሰቡ አካባቢውን እና የምርጫ ጣቢያዎችን ደኅንነት በመጠበቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም አሳስበዋል።

#አሚኮ #ምርጫ #መካነሰላም #አማራ #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleበ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ
Next articleበስድስቱም ምርጫዎች የተሳትፉት፤ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተዘጋጁት የጎንደር ከተማ ነዋሪ 🗳🇪🇹