🗳️ 🇪🇹 የአማራ ክልል ወጣቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን በምርጫው ንቁ ተሳታፊ ለመኾን መዘጋጀቱን ገለጸ።

5

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ተዓማኒ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ወጣቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የፌዴሬሽኑ ኘሬዝዳንት ግርማ አቸነፍ ፌዴሬሽኑ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ገለልተኛ የሲቪክ ማኅበር በመኾኑ የታዛቢነት ሚናውን ለመወጣት የተለያዩ ዝግጅቶችን አድርጓል ብለዋል።

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡም ሥራዎች መከናወናቸውን ነው የተናገሩት።

የምርጫ አስተባባሪዎችን እና ታዛቢዎችን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ሥልጠና በመስጠት ወደ እያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓልም ብለዋል።

የተሰማሩ ወጣቶች የሀገሪቱን ምርጫ ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ አቅጣጫ ተሰጥቷል፤ በዚህም 142 ምርጫ አስተባባሪዎች እና 1ሺህ 121 ታዛቢዎች መሰማራታቸውን ነው ያስረዱት።

ዜጎች ያለምንም ስጋት ድምፃቸውን የሚሰጡበት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፏቸውን እንዲወጡ ዝግጅት መደረጉንም ነው የተናገሩት።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ እና ተዓማኒ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የወጣቶች ሚና የጎላ እንደኾነም አስረድተዋል።

ፌዴሬሽኑ የምርጫ ተሳትፎው የክልሉን የፖለቲካ ብስለት እና የወደፊት ተስፋ የሚያሳይ ታሪካዊ ክስተት ኾኖ እንዲቀጥል የድርሻውን እየተወጣ ነውም ብለዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #ባሕር_ዳር #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !*

Previous article🗳️ 🇪🇹ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ መዋቅሩ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።
Next articleበ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ