🗳️ 🇪🇹ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ መዋቅሩ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።

3

 

ከሚሴ፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ኡመር መሀመድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ኹሉም የምርጫ ጣቢያዎች ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

ለምርጫው ስኬታማነት በቂ ሥልጠና ለፖሊስ አባላቱ መሰጠቱን ጠቅሰው ከሌሎች የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ማኅበረሰቡ ለምርጫው ስኬታማነት ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሥራት አጋርነቱን እንዲያረጋግጥም አሳስበዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ሞርጫ_2018 #ኦሮሞብሔረሰብ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጎንደር ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ እየተሠራጨ ነው።
Next article🗳️ 🇪🇹 የአማራ ክልል ወጣቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን በምርጫው ንቁ ተሳታፊ ለመኾን መዘጋጀቱን ገለጸ።