በጎንደር ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ እየተሠራጨ ነው።

5

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ በከተማዋ ተገኝቶ እንደተመለከተው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ የምርጫ ጣብያዎች እየተሰራጨ ነው።

የምርጫ ጣብያ አስተባባሪዎች ከማዕከል እየተረከቡ ወደ ጣብያዎቻቸው እያጓጓዙ ይገኛሉ። ለምርጫ ቁሳቁሱ ስርጭት አስተማማኝ የጸጥታ ጥበቃ እያደረገ ስለመኾኑም የከተማ አሥተዳደሩ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ አረጋግጧል። ሕዝቡም ምርጫውን በባለቤትነት ይዞ የአካባቢውን ሰላም በንቃት እየጠበቀ እና ስኬታማ ምርጫ ለማከናወን በመተባበር ላይ ነው።

#አሚኮ #ጎንደር #ምርጫ_2018 #ምርጫ

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article👨‍🎓🎓📚 በሰሜን ጎጃም ዞን ተማሪዎችን ለፈተና ለማብቃት ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
Next article🗳️ 🇪🇹ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ መዋቅሩ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።