👨‍🎓🎓📚 በሰሜን ጎጃም ዞን ተማሪዎችን ለፈተና ለማብቃት ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

10

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ2018 ዓ.ም ክልል አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን የሰሜን ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።

ተማሪዎችን ለማብቃት የተለያዩ ስልቶች በመዘርጋት
ልዩ ድጋፍ እየተደረገ መኾኑን የመምሪያው ምክትል ኀላፊ የሺወርቅ ድረስ ገልጸዋል።

እየተደረጉ ካሉ ድጋፎች መካከልም፦

👩‍🏫📚የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት።

🧠💪 የሥነ-ልቦና ድጋፍ የመስጠት እና ዝግጁ እንዲኾኑ የማድረግ።

📝መምህራን ለፈተና የሚያዘጋጁ ጥያቄዎችን የመሥራት እና የማብቃት።

🏛️ተማሪዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ቤተ-መጻሕፍት ክፍት ኾነው እንዲያገለግሉ የማድረግ።

👧ተማሪዎችን በደረጃ በመለየት ልዩ ድጋፍ የመስጠት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በዞኑ በበይነ-መረብ ፈተና የሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማዘጋጀት ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲለማመዱ እና የኮምፒውተር ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ እየተደረገም ነው።

የክልሉ መንግሥት ያደረገውን የኮምፒውተር ድጋፍ ለትምህርት ቤቶቹ የማዳረስ እና ኮምፒውተሮቹ ከኢንተርኔት መስመር ጋር እንዲገናኙ የማድረግ ሥራ እየተሠራ ነውም ብለዋል።

በዞኑ፦
👦👧 የ6ኛ ክፍል፦ 10 ሺህ 510 ተማሪዎች

📚 የ8ኛ ክፍል፦ 9 ሺህ 483 ተማሪዎች

👨‍🎓👩‍🎓 የ12ኛ ክፍል፦ 3 ሺህ 928 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ነው ያስረዱት።

​ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል ነው ያሉት። ተማሪዎችን ለማብቃትም ተሠርቷል ብለዋል።

ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ይመዘገባል ተብሎ ተስፋ ተጥሏልም ነው ያሉት። ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል።

#አሚኮ_ዜና #ትምህርት_የፈተና_ዝግጅት #ሰሜን_ጎጃም #ባሕር_ዳር #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleለአርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያ ስጋት አማራጭ መፍትሔ ተዘርግቷል።
Next articleበጎንደር ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ እየተሠራጨ ነው።