♿️ በጎንደር ከተማ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 🗳 በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።

3

 

ጎንደር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ ነዋሪ ከኾኑት አካል ጉዳተኞች መካከል አቶ እንዳልክ ተፈራ እና አቶ መሳፍንት ጌትነት ለአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ እንደተናገሩት ቀደም ሲል የምርጫ ካርድ ወስደው የምርጫውን ዕለት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

🗳️ እንደ አካል ጉዳተኛ በቀጣይ የሚያስፈልጋቸውን ልዩ ፍላጎት ለማሟላት በምርጫው በንቃት መሳተፍ ወሳኝ መኾኑን ይገልጻሉ። በዚህም የፊታችን ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

🗓️ ምርጫ የነገን እጣ ፈንታ ለመወሰን የሚያገለግል የዴሞክራሲ መሣሪያ በመኾኑ አካል ጉዳተኞችም የዜግነት ግዴታቸውን በምርጫ በመሳተፍ ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው የገለጹት።

#አሚኮ #ምርጫ2018 #ጎንደር #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ 🇪🇹የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።
Next articleለአርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያ ስጋት አማራጭ መፍትሔ ተዘርግቷል።