🗳️ 🇪🇹የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።

16

 

ደብረብርሃን፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ​የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ድምጽ ለመስጠት ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ምርጫው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገለጫ መኾኑን እና የእያንዳንዱ መራጭ ድምጽ እኩል ዋጋ እንዳለው ገልጸዋል።

በከተማዋ የሚገኙ ወጣቶች፣ ሴቶች እና አረጋውያን የመምረጥ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ነው ያረጋገጡት።

የምርጫ ጣቢያዎቹም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ኾነው ሊዘጋጁ እንደሚገባ አሳስበዋል።

መራጮች የሚወክላቸውን አካል በነፃነት እንደሚመርጡም ነው ያረጋገጡት።

ዘጋቢ፦ሥነጊዮርጊስ ከበደ
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ሞርጫ_2018 #ሰሜን_ሽዋ #ደብረ_ብርሃን #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !*

Previous article🗳️ ነጋችሁን በካርዳችሁ ምረጡ !
Next article♿️ በጎንደር ከተማ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 🗳 በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።