የሀገርን እጣ ፈንታ በካርዳቸው ለመወሰን መዘጋጀታቸውን የአብርሐጅራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

10

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብርሐጅራ ከተማ ነዋሪዎች ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጁ መኾናቸውን ለአሚኮ ተናግረዋል።

የአብርሐጅራ ከተማ ነዋሪ አቶ አስመቸ መለስ ዘንድሮ በመራጭነት የሚሳተፉት ለ4ኛ ጊዜ ነው። ባለፉት 3 የምርጫ ዘመኖች በመራጭነት መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። ለእሳቸው የዘንድሮው ምርጫ ልዩ ነው፤ ምክንያቱም “እኔና ባለቤቴን ጨምሮ 10 ልጆቻችን ጭምር በሙሉ የመራጭነት ካርድ ወስደናል። አሁን ሁላችንም ግንቦት 24/2018 ዓ.ምን በጉጉት እየጠበቅን ነው” ይላሉ።

አቶ አስመቸ የምርጫ ቅስቀሳው ለሀገር ሰላም እና ልማት ይጠቅማል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ጥሩ ግንዛቤ እንዳስጨበጣቸው በልበ ሙሉነት ይናገራሉ።

ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ አብራራው ሽፈራውም “የምርጫን ዋጋ ጠንቅቄ አውቃለሁ” ብለዋል። “በሕዝብ ይሁንታ የተመረጠ መንግሥት ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ ነው፤ እኛም የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ ነን” ብለዋል።

ዘጋቢ፦ቴዎድሮስ ደሴ

#አሚኮ_ዜና #ሞርጫ #ምዕራብ_ጎንደር #አብርሐጅራ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወጣቶች “የሰላም ዘብ እኔው ነኝ” በማለት ለስኬታማ ምርጫ እየሠሩ ነው።
Next article🗳️ 🇪🇹በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለምርጫው አስተማማኝ የጸጥታ ዝግጅት ተደርጓል።