🗳️ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወጣቶች “የሰላም ዘብ እኔው ነኝ” በማለት ለስኬታማ ምርጫ እየሠሩ ነው።

9

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፊታችን ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ ኾኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳደር አስታውቋል።

የዞኑ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ አንተነህ ታደሰ ለምርጫው ስኬታማነት የጸጥታ ሥራው በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫው ዕለት እና በድህረ ምርጫ የሚከናወኑ ተግባራት ተለይተው አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

ቀደም ሲል ለሁሉም የጸጥታ አካላት አስፈላጊው ግንዛቤ ተፈጥሮ በቂ የጸጥታ ስምሪት መደረጉንም ገልጸዋል። ማኅበረሰቡም የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ያለው ተነሳሽነት እና ንቁ ተሳትፎ ከፍተኛ መኾኑን ጠቅሰው አመስግነዋል።

በየደረጃው ያለው የጸጥታ መዋቅር ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት አስተማማኝ የጸጥታ ሥራ እየተከናወነ ስለመኾኑንም አብራርተዋል።

በተለይም ወጣቶች “የሰላም ዘብ እኔ ነኝ” በሚል አስተሳሰብ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በጋራ እየሠሩ መኾኑን ነው የተናገሩት።

በምርጫው ዕለትም መላው ሕዝብ በነጻነት ወጥቶ ለመምረጥ የሚያስችለውን አስተማማኝ የጸጥታ ዝግጅት መደረጉን ኀላፊው አረጋግጠዋል።

#አሚኮ #ማዕከላዊ-ጎንደር #ምርጫ_2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleሕይወታቸውን ያሻሽላል ያሉትን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የፋርጣ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
Next articleየሀገርን እጣ ፈንታ በካርዳቸው ለመወሰን መዘጋጀታቸውን የአብርሐጅራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።