
ደብረታቦር፡ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ አርሶ አደር እያሱ ዋለ፣ አርሶ አደር አደራ ጌትነት እና አርሶ አደር ደረሰ ውብአንተ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ በወቅቱ የመራጭነት ካርድ ማውጣታቸውን ለአሚኮ ተናግረዋል።
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ከጠዋት ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ ለመምረጥ ዝግጁ ኾነው እየተጠባበቁ መኾናቸውንም ነግረውናል።
በተካሄዱ የምርጫ ቅስቀሳዎች እና የማኒፌስቶ ትውውቆች ለአርሶ አደሮች የሚጠቅም ሀሳብ ያለውን ፓርቲ ለይተናል ብለዋል። የአርሶ አደሮችን ሕይወት ያሻሽላል፣ ሀገር ያሳድጋል ብለን ያሰብነውን ለመምረጥም ተዘጋጅተናል ነው ያሉት።
ማኅበረሰቡ መንግሥት በምርጫ እንጅ በግጭት መመሥረት የለበትም በማለት ከሰላም ጎን ኾኖ እየሠራ ነው ብለዋል። ለሰላም መስፈን እየሠሩ እንደሚገኙም አንስተዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅም ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን ኾነው እየሠሩ መኾናቸውን አረጋግጠዋል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #ደቡብ_ጎንደር #ፋርጣ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ 🇪🇹
ዘጋቢ፦አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
