🗳️ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ እየተሠራ መኾኑን የፈንድቃ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

7

 

እንጅባራ፡ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረስብ አሥተዳደር የፈንድቃ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኢንስፔክተር አደራጀው አሰፋ የፖሊስ አባላት በምርጫ ጉዳይ ላይ ሥልጠና ወስደው ወደ ተግባር መግባታቸውን ገልጸዋል።

ምርጫው ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅም ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ያነሱት ኀላፊው ከጃዊ ወረዳ ጋርም በቅንጅት እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል።

ምርጫው ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅም በጋራ እየገመገሙ እየሠሩ መኾናቸውንም ተናግረዋል።

ማኅበረሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተጣምሮ በመሥራት ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅም እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #አዊ_ፈንድቃ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹🗳

ዘጋቢ፦ሰለሞን ስንታየሁ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

  1. ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article🗳️ በደቡብ ጎንደር ዞን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስተማማኝ የጸጥታ ዝግጅት ተደርጓል።
Next articleሕይወታቸውን ያሻሽላል ያሉትን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የፋርጣ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።