🗳️ በደቡብ ጎንደር ዞን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስተማማኝ የጸጥታ ዝግጅት ተደርጓል።

5

 

ደብረታቦር፡ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን ፓሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ንጉስ ታመነ እንደተናገሩት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል፡፡

ኀላፊው የጸጥታ ኀይሉ ሙያዊ ሥነ ምግባርን ተላብሶ ሥራውን ሲሠራ መቆየቱን ተናግረው ፤ ምርጫው ሰላማዊ እንዲኾንም ጠንክሮ ይሠራል ብለዋል፡፡

የምርጫውን ፋይዳ በመረዳት ሙያዊ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡም ለሁሉም የፖሊስ አባለት የምርጫ ሥነምግባር ሥልጠና እንዲወስዱ ተደርጓልም ነው ያሉት።

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በምርጫ ቦርድ የወጡ ሕጎችን ተግባራዊ ለማድረግ ፓሊስ መሥራት ያለበትን ለይቶ እንዲሠራ በማድረግ በኩል ግንዛቤ መፈጠሩንም አክለዋል።

የምርጫ ጣቢያዎችን አካባቢ ደኅንነታቸው የተጠበቀ ለማድረግ እየሠሩ መኾናቸውንም ኀላፊው አጽንኦት ስጥተዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ፓሊስ መምሪያ ምክትል ኅላፊ እና የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ኅላፊ ኮማንደር አጉማስ አያሌው ፓሊስ በገለልተኛ ሥራዎችን ለማከናወን እና ተጨባጭ መረጃዎችን በመያዝ በምርጫ ወቅት እና ከምርጫ በፊት የሚስተዋሉ ጉዳዮችን በመከታተል ለምርጫው ሰላማዊነት በቅንጅት እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

ሕግ እና ሥርዓትን ለማረጋገጥ ከዞኑ ፍትሕ መምሪያ ጋር የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ኅብረተሰቡ ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን ከፖሊስ ጋር በጥምረት እንዲሠራም ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #ደቡብ_ጎንደር #ደብረታቦር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next article🗳️ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ እየተሠራ መኾኑን የፈንድቃ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።