🗳️ የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

9

 

ደብረማርቆስ፡ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት ዝግጁ መኾናቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ ሦስት ቀናት ብቻ በቀሩበት በዚህ ወቅት ዜጎች መብታቸውን ተጠቅመው ይበጀናል ለሚሉት ድምፃቸውን ለመስጠት ዕለቱን እየተጠባበቁ ነው፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎችም ይህን ምርጫ ሲጠብቁ መቆየታቸውን እና የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

በምርጫ ብቻ የሚመሠረት ቅቡልነት ያለው መንግሥት ብቻ እንዲኖረን ነው የምንፈልገው ያሉት ነዋሪዎቹ ይህን ለማረጋገጥም ምርጫ የሚካሄድበት ቀን እየተጠባበቁ መኾናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የሁሉም ነዋሪዎችም በዚህ ምርጫ ንቁ ተሳታፊ እንዲኾኑም ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

ነዋሪዎቹ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #ደብረ_ማርቆስ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የቻግኒ ከተማ ፖሊስ ጽሕፍት ቤት አስታወቀ።
Next article🗳️ በደቡብ ጎንደር ዞን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስተማማኝ የጸጥታ ዝግጅት ተደርጓል።