🗳️ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የቻግኒ ከተማ ፖሊስ ጽሕፍት ቤት አስታወቀ።

11

 

እንጅባራ፡ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የቻግኒ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፍት ቤት አስታውቋል።

የቻግኒ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፍት ቤት አዛዥ ኮማንደር አገኘሁ ጥሩነህ የፖሊስ ተቋሙ ከሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የሚደረገው የድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት በሰላም እንዲከናወንም አስፈላጊው የጸጥታ ስምሪትም መደረጉን ገልጸዋል። ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመናበብ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

ኅብረተሰቡ ለምርጫው ሰላማዊነት ከጸጥታ አካላት ጋር በመናበብ እንዲሠራ እና የተለመደ የሰላም አጋርነቱን እንዲያረጋግጥም አሳስበዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #አዊ_ቻግኒ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleለምርጫው ስኬታማነት መሥራት ሀገራዊ ኀላፊነትን መወጣት ነው።
Next article🗳️ የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።