ለምርጫው ስኬታማነት መሥራት ሀገራዊ ኀላፊነትን መወጣት ነው።

7

 

ደብረ ማርቆስ: ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ የጸጥታ ኃይሉ ሕግ እና ሥርዓትን በማስከበር ምርጫው በስኬት እንዲከናወን ኀላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል።

በከተማዋ የሚገኙ የጸጥታ አካላት ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ለምርጫው ስኬታማነት እየሠሩ መኾኑን የገለጹት ደግሞ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ይሄነው አበባው ናቸው።

ሰላምን የማስጠበቅ ሂደት ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ባለመኾኑ ማኅበረሰቡ ከጸጥታ አካላት ጎን ኾኖ ኀላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
Next article🗳️ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የቻግኒ ከተማ ፖሊስ ጽሕፍት ቤት አስታወቀ።