🗳️ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነው።

4

 

ደሴ፡ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ ሦሥት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሰኢድ አሊ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

ማኅበረሰቡ በምርጫ ወቅት ሰላሙን እንዲጠብቅ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ መከናወኑንም ጠቁመዋል።

የጸጥታ መዋቅሩ ከሕዝብ ጋር በመተባበር የምርጫ ጣቢያዎችን እና የከተማዋን ሰላም እየጠበቀ መኾኑንም ተናግሯል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በከተማዋ ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነውም ብለዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #ኮምቦልቻ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleለምርጫው ስኬታማነት ትርጉም ሰጥቶ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ የፍኖተ ሰላም ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።
Next articleለምርጫው ስኬታማነት መሥራት ሀገራዊ ኀላፊነትን መወጣት ነው።