ለምርጫው ስኬታማነት ትርጉም ሰጥቶ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ የፍኖተ ሰላም ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።

3

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገርን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት፤ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ እና የሕዝብን እውነተኛ ፍላጎት ለማሟላት ምርጫ መሠረታዊ ነው።

የፍኖተ ሰላም ከተማ ወጣቶችም በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ሂደት ላይ የበኩላቸውን አሻራ ለማሳረፍ እየተዘጋጁ ነው።
ሁሉም ማኅበረሰብ በምርጫው ንቁ ተሳታፊ መኾን እንዳለበት የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪው ወጣት ተመስገን አድማሱ ተናግሯል።

ሌላኛው ወጣት በላይነህ አበበ ወጣቶች የያዙትን የምርጫ ካርድ በአግባቡ በመጠቀም በድምጽ መስጫው ቀን የራሳቸውን የወሳኝነት ሚና መወጣት አለባቸው ብሏል።

ለምርጫው ስኬታማነት ትርጉም ሰጥቶ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ያለው ደግሞ ወጣት ገብረ ሕይወት ዓለሜ ነው።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ድምጽ ከመስጠት ጎን ለጎን ሰላምን መጠበቅ ከሁሉም እንደሚጠበቅም አንስቷል።

#ስኬታማ-ምርጫ #ፍኖተ-ሰላም #ምርጫ2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ በቅንጅት መሥራት ለምርጫው ስኬታማነት ወሳኝ ነው፡፡
Next article🗳️ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነው።