🗳️ በቅንጅት መሥራት ለምርጫው ስኬታማነት ወሳኝ ነው፡፡

5

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ በሰፊ ዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡ በጅንካ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ምስክር ከተማ ምርጫ የአንድ ሀገር ሕዝብ ሥልጡንነት ማሳያ ነው ብለዋል።

ምርጫ ሲካሄድ የራሱ ሂደት አለው የሚሉት መምህሩ ይህን ሂደት ሰላማዊ ማድረግ ምርጫውን በውጤታማነት ለመፈጸም ሁነኛ መንገድ እንደኾነ ነው የገለጹት።

ሰፊ ዝግጅት እያደረገች የምትገኘው ኢትዮጵያም ሰላማዊ የምርጫ ሂደት እያከናወነች እንደምትገኝ መታዘባቸውን አስረድተዋል፡፡

በተለይም የተፎካካሪ ፓርቲዎች አሁን ላይ የምርጫውን ሂደት ሰላማዊ ለማድረግ እየተመካከሩ የሚሠሩት ሥራ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁኔታዎች በእጅጉ እንደሚለይ እና ምርጫውን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ በሚደረገው ጥረት አጋዥ እንደኾነ ጠቁመዋል፡፡

በምርጫው ሂደት ላይ ፓርቲዎች የምርጫ ቦርድ ሕግ እንዲከበር የማድረግ ኀላፊነት እንዳለባቸው ነው የተናገሩት። ለዚህም በጋራ መሥራት ይገባል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ የሚገኘውን የምርጫ ውጤትም በጸጋ መቀበል ከሁሉም ፓርቲዎች እና ከደጋፊዎቻቸው እንደሚጠበቅም ነው የፖለቲካ መምህሩ የገለጹት፡፡

#አሚኮ_ዜና #ምርጫ2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleበድምጻቸው ለመወሰን መዘጋጀታቸውን የባሕር ዳር ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next articleለምርጫው ስኬታማነት ትርጉም ሰጥቶ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ የፍኖተ ሰላም ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።