
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 21/2018 (አሚኮ) የፊታችን ሰኞ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፃችንን በመስጠት ለመወሰን ተዘጋጅተናል ሲሉ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ከ50 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፃቸውን ለመስጠት ካርድ የወሰዱበትና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ሰኞ ድምፅ የሚሰጥበት ይሆናል።
በዚህም መሰረት በወሰዱት ካርድ ድምፃቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን በባሕር ዳር ከተማ ኢዜአ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አስተያየታቸውን ከሰጡት ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ትዕግስት አበጀ፣ አቶ ገብረስላሴ ሳህሌ እና ደጀኔ አለምነው፤ ቀናቶች በቀሩት የምርጫ እለት ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል ብለዋል።
የወሰድነው ካርድ ዋጋ የሚኖረው ድምጽ ስንሰጥ ብቻ በመሆኑ በእለቱ በመገኘትና ድምፅ በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።
#በምርጫብቻ #ኢትዮጵያትመርጣለች #Ethiopia #ምርጫ #AMECO
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
