🗳️ በምርጫ ክርክሩ የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያበቃ ግብዓት እንዳገኙ የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

3

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ መገናኛ ብዙኅንን በመጠቀም የምርጫ ክርክር፣ የምረጡኝ ቅስቀሳ እና የምርጫ ምልክት የማስተዋወቂያ መርሐ ግብሮችን አካሂደዋል።

በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎችም በፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር እና የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ ለውሳኔ የሚያበቃቸውን መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በምርጫው ዕለት ካርዳቸው ሳይባክን ይመራናል ለሚሉት ፓርቲ ድምጽ ለመስጠት ዝግጁ መኾናቸውንም ገልጸዋል።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃ እና ዲሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #አዊ_ቻግኒ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ ሕዝብ ድምጹን በነጻነት እንዲሰጥ የጸጥታ ኃይሉ ኀላፊነቱን ይወጣል።
Next articleበድምጻቸው ለመወሰን መዘጋጀታቸውን የባሕር ዳር ነዋሪዎች ተናገሩ።