🗳️ ሕዝብ ድምጹን በነጻነት እንዲሰጥ የጸጥታ ኃይሉ ኀላፊነቱን ይወጣል።

5

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲከናወን በቂ ዝግጅት ማድረጉን የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ አስታውቋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኅላፊ ደረሰ አዱኛ ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ከሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ከክልሉ የጸጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት ለምርጫው ስኬታማነት በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

በሁሉም ወረዳዎች እና ከተሞች የሰላም ዘብ ወጣቶችን በማሠልጠንም ተግባራትን እንዲያግዙ ተደርጓል ነው ያሉት።

የጸጥታ ኃይሉ እና ሕዝቡ በጋራ በሠሩት የተቀናጀ ተግባር በዞኑ ያለው ሰላም የተሻለ መኾኑን ነው የተናገሩት።

በቀጣይም በጋራ በመቀናጀት ልማትን እና ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ እየሠራን ነው ብለዋል። ስኬታማ ምርጫንም ለማስኬድ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

“ሕዝቡ ድምጹን በነጻነት ይሰጥ ዘንድ የጸጥታ ኃይሉ ኀላፊነቱን ይወጣል” ነው ያሉት።

#አሚኮ-ዜና #ምዕራብ-ጎንደር #ምርጫ2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ የለም።
Next article🗳️ በምርጫ ክርክሩ የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያበቃ ግብዓት እንዳገኙ የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።