🗳️ 🇪🇹በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለምርጫው አስተማማኝ የጸጥታ ዝግጅት ተደርጓል።

22

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ​ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በቂ የጸጥታ ዝግጅት ማድረጉን የዞኑ የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ አስታውቋል።

የመምሪያው ኀላፊ አወል እንድሪስ እንደገለጹት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የተቀናጀ የጸጥታ መዋቅር ተገንብቶ ወደ ሥራ ገብቷል። ለምርጫው የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ወደየጣቢያዎቹ የማሰራጨት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

ኅብረተሰቡም ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የራሱን ሰላም እየጠበቀ መኾኑን የገለጹት ኀላፊው በምርጫው ዕለት መራጩ ሕዝብ በነፃነት ወጥቶ ድምጽ የሚሰጥበት አስተማማኝ ሁኔታ መፈጠሩንም አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ሞርጫ_2018 #ኦሮሞብሔረሰብ_ከሚሴ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየሀገርን እጣ ፈንታ በካርዳቸው ለመወሰን መዘጋጀታቸውን የአብርሐጅራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next article🗳️ ነጋችሁን በካርዳችሁ ምረጡ !