🗳️በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

26

 

ጎንደር፡ ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አሚኮ ያነጋገራቸው የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አቶ ሸረፈዲን ኢብራሂም፣ አቶ ዘሪሁን በሪሁን እና አቶ አምበል ብርሃኔ ለአሚኮ እንደተናገሩት ካርድ አውጥተው የምርጫውን ቀን አየተጠባበቁ ይገኛሉ።

የተሻለ ዴሞክራሲን ለመገንባት በምርጫው በንቃት መሳተፍ ወሳኝ መኾኑንም ነው አስተያየታቸውን የሰጡት።

በምርጫ መሳተፍ የዜግነት ግዴታ መኾኑን በመገንዘብ የያዙትን ካርድ በአግባቡ እንደሚጠቀሙበትም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ አካባቢውን በመጠበቅ እና ከሚመለከተው የጸጥታ ኀይል ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት ሰላሙን የመጠበቅ ኀላፊነቱን መወጣት እንደሚኖርበትም አስተያየታቸውን አጋርተውናል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #ጎንደር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ በእንጅባራ የሚገኙ መምህራን በምርጫው ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።
Next article“ስኬታማ ምርጫ እንዲከናወን ታሪካዊ ኀላፊነታችንን እንወጣለን” የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች