🗳️ በእንጅባራ የሚገኙ መምህራን በምርጫው ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።

28

 

እንጅባራ፡ ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በእንጅባራ ከተማ የሚገኙ መምህራን የምርጫ ካርድ ወስደው ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

መምህራኑ በተለያዩ ሚዲያዎች የተላለፉ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ፖሊሲዎች እና ዓላማዎች በመከታተል ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ነው ያስረዱት።

እያንዳንዱ ድምጽ ዋጋ ስላለው መራጮች በዕለቱ ወጥተው ድምጽ መስጠት አለባቸው ብለዋል።

በተጨማሪም ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ እና የፖለቲካ ፓርቲዎችም የምርጫውን ውጤት በጸጋ መቀበል እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #አዊ_እንጅባራ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ በቃሉ ፈረደ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ኾኖ እንዲካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዝግጅት አድርጓል።
Next article🗳️በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።