7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ኾኖ እንዲካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዝግጅት አድርጓል።

15

 

አዲስ አበባ: ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር የጥሞና ጊዜ ማብሰሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተመረጡ ርዕሶች ላይ ክርክር ሲያደረጉ መቆየታቸውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሠብሣቢ ተስፋዬ ንዋይ ተናግረዋል።

የክርክር ሂደቱ የሲቪክ ማኅበረሰብ፣ የትምህርት ተቋማት እና የግል ሠራተኞችን ያሳተፈ ሲኾን ታዳሚያን ለፓርቲዎች ጥያቄዎችን እንዲያነሱ መደረጉንም ተናግረዋል።

በክርክር ሂደቱ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ንቁ ተሳታፊ መኾናቸውንም አንስተዋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ምርጫው ፍትሐዊ ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ኾኖ እንዲካሄድ እየሠራ መኾኑን የተናገሩት ደግሞ የቦርዱ ሠብሣቢ ሜላተወርቅ ኀይሉ ናቸው።

በዚህም ከዛሬ ግንቦት 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ የጥሞና ጊዜ ኾኖ መወሰኑንም ገልጸዋል።

በምርጫው ለሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መልካም ዕድል በመመኘት የምርጫ ውጤቱን በሠለጠነ እና ሰላማዊ በኾነ መንገድ በመቀበል ለኢትዮጵያ ልማት በጋራ እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ሠብሣቢዋ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ገልጸዋል።

በምርጫ ሂደቱ ማንኛውንም መረጃ መስጠት ካስፈለገ 6214 ነፃ የስልክ መስመር አለያም 7555 በአጭር የጽሑፍ መልዕክት መስጫ ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል አመላክተዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #ምርጫ_ቦርድ #አዲስ_አበባ #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ: ሰላማዊት ነጋ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ “ለምርጫው ስኬታማነት በቂ ዝግጅት ተደርጓል” የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ
Next article🗳️ በእንጅባራ የሚገኙ መምህራን በምርጫው ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።