🗳️ “ለምርጫው ስኬታማነት በቂ ዝግጅት ተደርጓል” የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ

13

 

ጎንደር: ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ምርጫው ስኬታማ ኾኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አስታውቋል።

የከተማ አሥተዳደሩ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ አለልኝ ዓለም ለምርጫው ስኬታማነት የጸጥታ ሥራው በምርጫው ዕለት እና ከምርጫ በኋላ የሚከናወኑ ተግባራት ተለይተው አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንና ወደተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

እያንዳንዱ የጸጥታ መዋቅር ከኅብረተሰቡ ጋር ተሰናስሎ ለጋራ ሰላም በትብብር እየሠራ እንደኾነም ነው የገለጹት።

🕊️ ማኅበረሰቡ “ሰላሜ የእኔ ነው” በሚል እሳቤ አጋዥ ኾኖ እየሠራ ነው ብለዋል።

ለጸጥታ መዋቅሩ መረጃ የመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

#አሚኮ #ጎንደር #ምርጫ_2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች በምርጫ ሀገራዊ ኀላፊነታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።
Next article7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ኾኖ እንዲካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዝግጅት አድርጓል።