
እንጅባራ: ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ አራት ቀናት ብቻ በቀሩት በአሁኑ ወቅት፣ በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ አውጥተው ግንቦት 24/2018 ዓ.ምን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
የከተማዋ ነዋሪ አቶ ጌታው ስንታየሁ፣ ወርቅነሽ አጋጄ እና አቶ አለበል ጥላሁን ለአሚኮ እንደገለጹት የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት እና ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
የፓርቲዎችን ቅስቀሳ በአግባቡ መከታተላቸውን የጠቀሱት ነዋሪዎቹ ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #እንጄባራ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ፦ ሰለሞን ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
