ማንኛውም ተዘዋዋሪም ሆነ ተቀማጭ የዕጩ ወኪሎች ግዴታዎች፦

13

 

1. የምርጫ ኃላፊው የሚሰጠውን ትዕዛዞች ማክበር አለበት፣
2. የምርጫ ሂደቱን ከሚያውኩ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣
3. አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅ መታወቂያውን ማሳየት አለበት፣
4. የምርጫ ሕጉን ማክበር አለበት፣
5. የምርጫውን ሂደት የመከታተል ተግባሩን ሲያከናውን መራጮች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው አስተያየት ከመስጠት ወይም ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር የለበትም፣
6. የምርጫ ቁሳቁሶችን መያዝ፥ ማንሳት፤ መነካካት ወይም በቁሳቁሶቹ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተግባራትን መፈጸም የለበትም፣
7. የምርጫ ጣቢያውን ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ከማስፈራራት ወይም ሥራውን ከሚያደናቅፉ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣
8. ወደ ድምፅ መስጫ ክፍሎች መግባት የለበትም፣
9. ቦርዱ የሚያወጣውን የሥነ ምግባር ደንብ መፈረም እና ማክበር ይገባዋል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 121 መሠረት ማንኛውም ተዘዋዋሪም ሆነ ተቀማጭ የዕጩ ወኪሎች እነዚህን ግዴታዎች ማክበር አለባቸው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“በክልሉ የተሻለ ሰላም መፈጠሩ ሕዝቡ በሙሉ አቅም እንዲያለማ አስችሏል።” እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)
Next articleየእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች በምርጫ ሀገራዊ ኀላፊነታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።