“በክልሉ የተሻለ ሰላም መፈጠሩ ሕዝቡ በሙሉ አቅም እንዲያለማ አስችሏል።” እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)

11

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር) እንደገለጹት ጠንካራ ሀገር ለመገንባት፣ ዴሞክራሲን ለማስፈን እና ልማትን ለማፋጠን ሰላምን ማረጋገጥ ቀዳሚው ተግባር ነው። ለዚህ ደግሞ የኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።

ኅብረተሰቡ የሀገሩን ክብር፣ የራሱን ሰላም እና ነጻነት የሚጋፉ አካላትን በጋራ ሊከላከል ይገባል። በተለይም በሀገር እና በልጆች የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ከሚመጣ ጠላት ጋር ድርድር ሊኖር እንደማይገባም አሳስበዋል።

በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኀይሎች ጥያቄዎቻቸውን በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተሰጣቸውን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባልም ነው ያሉት። ኅብረተሰቡም እነዚህ ኀይሎች ወደ ሰላም መስመር እንዲመጡ የበኩሉን ጥረት ማድረግ አለበት ብለዋል።

የጥፋት መንገድ እንደማያዋጣ ተገንዝበው በርካቶች ወደሰላም ተመልሰዋል፤ እየተመለሱም ነው ብለዋል። በዚህም በክልሉ የተሻለ ሰላም መፈጠሩን እና ሕዝቡም እፎይታ ማግኘቱን ዶክተር እሸቱ ገልጸዋል። “በክልሉ የተሻለ ሰላም መፈጠሩ ሕዝቡ በሙሉ አቅም እንዲያለማ አስችሏል” ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ የተሻለ ሰላም መኖሩን የጠቀሱት ዶክተር እሸቱ የሱፍ ሕዝቡ ይህንን የተገኘ ሰላም በንቃት እየጠበቀ ፊቱን ወደ ልማት እና ድህነትን ወደ ማጥፋት ማዞር እንዳለበት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

#አሚኮ_ዜና #ሰላም #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ሕዳሴ ግድብ የጽናት እና የጋራ ዕድገት ማረጋገጫ ነው” የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ
Next articleማንኛውም ተዘዋዋሪም ሆነ ተቀማጭ የዕጩ ወኪሎች ግዴታዎች፦