
ፍኖተ ሰላም፡ ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን የጸጥታ መዋቅር ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁን የዞኑ የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር አዱኛ አዳሙ አስታውቀዋል። የጸጥታ ኅይሉ ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝም ኮማንደር አዱኛ አረጋግጠዋል።
የምርጫ ቁሳቁሶችን እስከ ምርጫ ጣቢያዎች ድረስ ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ አጅቦ በስኬት ለማጓጓዝም ዝግጅቱ ተጠናቅቋል ነው ያሉት።
ሕዝቡ በነጻነት እንዲመርጥ የጸጥታ ኃይሉ በፍጹም ገለልተኛነት እና የምርርጫ ቦርድ መመሪያ በሚፈቅደው ርቀት ላይ ኾኖ ሥራውን እንደሚያከናውንም ገልጸዋል።
ከሕዝቡ ጋር ውይይቶች ተደርገዋል፤ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል በጋራ በመሥራት ምርጫውን በስኬት ለማጠናቀቅም መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጊዜው ደግአረገ ለምርጫው በስኬት መጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
የምርጫው ባለቤት መላው ሕዝብ እንደመኾኑ፤ በስኬት እንዲከናወንም ሕዝቡ ለሰላሙ ለጸጥታ ኀይሉ የላቀ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።
#አሚኮ_ዜና #የሰላም_ሥራ #ፍኖተ_ሰላም #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
