ከሚሴ፡ ግንበት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በከሚሴ ከተማ እየተከበረ ነው።
በበዓሉ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እስልምና ጉዳዮች የኡለሞች ምክር ቤት አባል የሆኑት ሼህ ያቁት ሼህ መሐመድ ሰይድ በዓሉ የመተባበር እና የመረዳዳት በመኾኑ በአብሮነት ማክበር ይገባል ብለዋል።
በእርድ ሥነ ሥርዓት ወቅትም ለአቅመ ደካሞች የሚሰጠውን በተገቢው ማድረስ እንደሚገባም አስረድተዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በመረዳዳት እና እርስ በእርስ በመጠያየቅ ሊያከብር እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ለሰላም ያሳየውን ትብብር በማስቀጠል መኾን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የበኩሉን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።
የከሚሴ ከተማ የሃይማኖቱ ተከታዮችም በዓሉን በመረዳዳትና በመጠያየቅ እንደሚያከብሩ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
#አሚኮ #ከሚሴ #ኢድአልአደሃ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
