የኢድ አል አደሃ በዓል በደብረ ታቦር ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

5

 

ደብረታቦር፡ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ 1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ በዓል በስግደት፣ በሶላት እና በሃይማኖታዊ አስተምህሮ እየተከበረ ይገኛል።

የደብረ ታቦር መስጊደል ኡስማን ኢማም ሀጅ ሸፈቀ መሐመድ የዒድ አል አደሃ በዓል የደስታ እና የመተዛዘን በዓል ኾኖ ከዚህ ደርሷል ብለዋል።

በበዓሉ ከሚታረደው መስዋዕት ለሌላቸው በማካፈል፣ በማዘን እና በመዋደድ የሚከበር እንደኾነ ነው የገለጹት። ቂም የያዘ ቂሙን ሽሮ የሚያከብረው የምሕረት በዓል መኾኑንም ተናግረዋል።

በኢድ አል አደሃ በዓል ተከፍቶ የሚያሳልፍ ሰው ሊኖር እንደማይገባ እስላማዊ አስተምህሮው ያዛል ያሉት ኢማሙ የከተማዋ ሙስሊም ማኅበረሰብ የሚያርደውን ለሌላቸው በማካፈል በደስታ እንዲውሉ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የደብረ ታቦር ከተማ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ሠብሣቢ ሀጅ ሙላት መሐመድ የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ከበዓላት ውጭም የመተሳሰብ፣ የመቻቻል እና የመተዛዘን የቆየ ባሕል አላቸው ብለዋል።

የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎችም ከሌሎች የሃይማኖት ተቋማት እና አማኞች ጋር በፍቅር እና በመዋደድ የሚኖሩ መኾናቸውን ገልጸዋል።

ከአደባባይ በዓሉ በኋላ እርድ በማከናወን ለሌላቸው ሰዎች ማዕድ የማጋራት ተግባር እንደሚከናወንም ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleበሰሜን ወሎ ዞን በ20 ቢሊዮን ብር የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት እየተከናወኑ ነው።
Next article“ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ለሰላም ያሳየውን ትብብር በማስቀጠል መኾን አለበት”