በሰሜን ወሎ ዞን በ20 ቢሊዮን ብር የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት እየተከናወኑ ነው።

5

 

ወልድያ: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ የተሠሩ የልማት ተግባራትን ተመልክተዋል።

የኮሪደር ልማት፣ የአውቶብስ መናኽሪያ፣ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ እና ድልድይ ግንባታን ጎብኝተዋል፤ ሥራም አስጀምረዋል።

የመርሳ ከተማ ከንቲባ ሙሐመድ ሰይድ በኅብረተሰቡ ድጋፍ እና በከተማው ሙሉ አቅም የአውቶቡስ መናኽሪያ እና 4 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት እየተሠራ መኾኑን አስረድተዋል።

የትምህርት ቤት ማስፋፊያው እና የድልድይ ግንባታው በፌዴራል መንግሥት በጀት ድጋፍ እየተሠራ መኾኑን ነው የገለጹት።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር በዞኑ ውስጥ 20 ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘላቸው 502 የልማት ኘሮጀክቶች እየተሠሩ ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ቢሮ ኀላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር) 64 ሜትር ርዝመት ያለው መገናኛ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ በፌዴራል መንገዶች ባለሥልጣን በተመደበ 100 ሚሊዮን ብር የበጀት ድጋፍ የተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

በከተማ አሥተዳደሩ የሚሠሩ የልማት ተግባሮች አበረታች መኾናቸውንም ነው የገለጹት።

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሐ ደሳለኝ ኘሮጀክቶቹ የብልጽግና ፓርቲን የመሥራት እና የመፈጸም አቅም የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የነጌሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን መረቁ።
Next articleየኢድ አል አደሃ በዓል በደብረ ታቦር ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።